የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በሲኖዶስ ጉባዔ ታደሙ

Views: 154

ከኢትዮጵያ ቤተክህነት የተነጠለ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለመመሥረት በክልላችን የሚደረገውን እንቅስቃሴ አንደግፍም፤ የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ በመሆኑ በመንግሥት መቼም ተቀባይነት አይኖረውም ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ተናገሩ፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጋር መንግሥትን ወክለው በምዕላተ ጉባዔው ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በተሳተፉበት ወቅት ‹‹ችግሮችም ካሉ ባፋጣኝ እናስተካክላለን፤ ከእናንተ ከአባቶቻችን ጋር በጋራ መስራት እንፈልጋለን›› ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት በተካሄደው አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ችግሮች ተብለው በተለዩ ሰባት ነጥቦች ላይ በዝግ ምክክር ተደርጓል፡፡
ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት እና የታረዱ ካህናት የፈሰሰው ደምና እንባ በጸሎት ተዘክሯል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹አባቶቼ ቤተክርስቲያን ብቻ አይደለችም የተቃጠለችው፣ የ3000 ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ጭምር እንጂ፤ ታዲያ ታሪክ ሲቃጠል መንግሥት እንዴት ዝም ይላል›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በጉባዔው ላይ የተሳተፉ አባቶች ለመንግሥት ተወካይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com