አቶ ክቡር መንግሥት ግዙፍ የልማት ድርጅቶችንእንዳይሸጥ አስጠነቀቁ እንዳይሸጥ

Views: 111

የአዲስ አበባና የክልል ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዝዳንት የነበሩት አንጋፋው የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ክቡር ገና፣ መንግሥት ግዙፍ የመንግሥት የልማት ተቋማትን ለመሸጥ መወሰኑ ስህተት ነው፤ ‹‹ባንሸጠው አንሞት›› በሚል መንግሥትን በመወትወት ላይ ናቸው፡፡
አቶ ክቡር ገና እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ባንኮች፣ የባህርና ትራንዚት አገልግሎት የመሳሰሉ ግዙፍ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን መሸጥ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ሲሉ የተለያዩ መከራከሪያ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡
እንደ ቴሌ ያሉ ግዙፍ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለግሉ ዘርፍ ቢሸጡ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል፤ ምክንያቱም የመንግስት ሀብት ለግል ሲዞር የአገልግሎትም ሆነ የዕቃ ዋጋ ይጨምራል፤ በአንፃሩ ደግሞ ጥራት ይቀንሳል ምክንያቱም ለትርፍ ስለሚሰሩ ነው ሲል ገልጿል፡፡
መጀመሪያውኑ ተቋማቱን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር የተወሰነው ልምድ በሌላቸው ወጣት የኢኮኖሚ አማካሪዎች ግፊት ሲሆን ሐምሌ 27 ቀን 2010 ዓ.ም የተቋቋመውና 21 አባላት ያለው የፕራይቬታይዜሽን አማካሪ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ምን እንዳማከረ ለህዝብ አልተነገረም ብለዋል፡፡
መንግሥት በ2010 ዓ.ም ከልማት ድርጅቶች ካተረፈው 45 ቢሊዮን ብር ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው ከኢትዮ ቴሌኮም ሲሆን፣ 30 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡
ስለዚህ፣ እነዚህን የልማት ድርጅቶች መሸጥ ማለት “ለመንግሥት ገቢ የምታስገባን የወተት ላም አሳልፎ እንደመስጠት ነው፡፡” ከመሸጥ ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ በአፍሪካ ደረጃ የሚሰሩ ተቋማት ማድረግ እንችላለ፡፡
መንግሥት ለልማት ድርጅቶች ምቹ ከባቢያዊ የስራ ድባብ ከፈጠረ ድርጅቶቹ የስራ አፈፃፀማቸውን ትርጉም ባለው መልኩ ያሻሽላሉ ሲሉ አቶ ክቡር ገልጸዋል፡፡
እነዚህን የልማት ድርጅቶች በመሸጥ ሀገሪቷ ያለባትን ዕዳ በሚገኘው ገንዘብ ማቃለል እንደሚቻልና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የተደገፈ አገልግሎት ለህዝቡ እንዲደርስ ማድረግ እንደሚቻልም በመንግስት በኩል ተነግሯል፡፡
“ይህ ንፋስ አመጣሽ ገንዘብ ለሀገሪቷ እንደ ህመም ማስታገሻ ኪኒን ነው የሚሆነው፡፡” ምክንያቱም ተቋማቱ በመንግስት ስር እያሉ የሚያስገቡት ገቢ በሙሉ የትም ሳይሄድ ለመንግስትና ለህዝብ ነው የሚሆነው፤ ነገር ግን የውጭ ባለሀብቶች እጅ በሚሆንበት ወቅት ገቢው ሁሉ ለውጭ ባለሀብት ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አሁንም ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com