የትኛውም የፖለቲካ ጥያቄ ፖለቲካዊ መፍትሔ አለው

Views: 147

የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበርና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ፣ በሀገሪቱ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለምርጫ የተደላደለ አይደለም፤ የፖለቲካ ምኅዳሩም በተለያዩ ክልሎች ተንቀሳቅሰን ለመስራት የሚያስችል አይደለም ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገለጹ፡፡

ምርጫው የሚካሄድበት ጊዜ ይራዘም አይራዘም የሚለውን ምክር ቤቱ ሊወያይባቸው ካሰበባቸው ሰባት አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ውይይት ከተደረገበት በኋላ የፓርቲዎቹን አቋም ለህዝቡ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡

“ምርጫው በጊዜው ካልተደረገ መሬት ትርዳለች ብሎ ማሰብ ተገቢ አይደለም” ስለዚህ፣ ለምርጫው የተመቻቸ ሁኔታ ስለሌለ ተወያይተንበት ቢወሰን የሚል አቋም እንደ ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አለን ብለዋል፡፡

የትኛውም የፖለቲካ ጥያቄና ችግር ፖለቲካዊ መፍትሔ አለው፤ ፖለቲካው የሚኖረው ለሰው ልጅ የተሻለ ህይወት ለመፍጠር ነው እንጂ ወደ ብጥብጥና ቀውስ የሚወስድ ነገር ከሆነ ግን ምርጫውም ሆነ ሌላው ጉዳይ መቆየት ይችላል ሲሉ አቶ ግርማ ለኢትዮ ኦንላይን ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር በአሁኑ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ይህን ችግር ሁላችንም ልናስተካክለው ይገባል፡፡

የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ራሱ ፈተና ውስጥ ነው ያለው፤ ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ በመጀመሪያ ከተስተካከለ ለምርጫው መቼ መካሔድ እንዳለበት መልስ ይኖረዋል ብለን እናስባለን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት እንደሚከናወን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

Comments: 1

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com