ዐራተኛው ፓትሪያርክ አንድ ሚሊዮን ብር ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት እድሳት እንዲውል ለገሡ

Views: 188

9የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐራተኛው ፓትሪያርክ ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ፣ ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተዘጋጀላቸው የበዓለ-ሲመት ፕሮግራም ላይ ለተለያዩ ወጪዎች ሊውል የነበረን አንድ ሚሊዮን ብር በተለያዩ አካባቢዎች ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት ግንባታ እንዲውል አደረጉ፡፡

ይህ የበዓለ-ሲመት ፕሮግራም፣ ከዚህ ቀደም በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚደረግ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያኗ በሚከበርበት ወቅት ለልዩ ልዩ ወጪዎች፡ ለወንበር፣ ለመጽሔት እና ለዝግጅት የሚወጣውን አንድ ሚሊዮን ብር፣ ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት እንዲውል እና ፕሮግራሙ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ እንዲከበር ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ እንዳደረጉ ተነግሯል፡፡

በዕለቱ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይም፣ አባታዊ መልዕክታቸውን የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊና የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሆኑት በብፁህ አቡነ ዮሴፍ አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ላይ እንዳሉት፣ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጡር ስለሆነ በተለያዩ ዓለማት ያሉ ህዝበ ክርስቲያናት በአንድ መንፈስ ሆነን የቤተክርስቲያናችንን ተቋማዊ እድገት፣ የህዝባችንን አንድነት በማስቀጠል፣ የተራቡትን በማብላት፤ የታረዙትን በማልበስ፤ ወላጆቻቸው ያለፉትን በማገዝ፤ የታመሙትን በመጠየቅ፤ የታሰሩትን ደግሞ በመጠየቅ፤ እንዲሁም ፍትሕ ያላገኙትን ግፉዓን ፍትሕ እንዲያገኙ በማድረግ፤ በሠላም እና በፍቅር ለመኖር አንድ ልብ ሆነን በፀሎት መትጋት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com