ዜና

ፓትሪያርኩ አዱሱን ዓመት ከጥላቻና ዘረኝነት ጸድተን እንቀበለው አሉ

Views: 226

ፓትሪያርኩ፣ “የኢትዮጵያ ህዝብ በአዲሱ ዓመት በውስጡ ያለውን ጥላቻና ዘረኝነት አፅድቶ በአዲስ መንፈስ፤ በፍቅርና በአንድነት ዓመቱን በጋራ ልንጀምረው ይገባል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ፓትሪያርኩ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐራተኛው ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በልዩ- ልዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች በድምቀት በተከበረበት ወቅት ነው፡፡

በበዓለ ሲመቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖትን ጨምሮ የየሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳሳትና የየአጥቢያው አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ይህ ዝግጅት አንድም ከ31 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የተዘጋጀ በዓለ ሲመት ፕሮግራም ሲሆን፣ በሌላ በኩል ለሁለት ተከፍሎ የነበረው ሲኖዶስ አንድ የሆነበት አንደኛ ዓመት ክብረ በዓልም ነው ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com