የንባብ ባህል ሳምንት በዛሬው ዕለት ተከፈተ፡፡

Views: 142

ስድስት ኪሎ የካቲት 12 የሰማእታት መታሰቢያ ሀውልት አደባባይ ከነሀሴ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የንባብ ባህል ሳምንት በዛሬው ዕለት ተከፈተ፡፡

የንባብ ሳምንቱን የከፈቱት የባህል፣ ኪነ–ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዮ ባዬ ናቸው፡፡

በመክፈቻው ላይም ረዳት ፕሮፌሰሩ ፤ የቀደሙት አባቶቻችን ሀገር በቀል እውቀቶችን ከትውልድ ትውልድ የሚያስተላልፉባቸው የራሳቸውፉ የሆነ ስልትና ስርዓት ነበራቸው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ቀለም በጥብጠው ብራና ፍቀው የሚጽፏቸውን እውቀቶች ከእነሱ ቀጥሎ ያለው ትውልድ የሚቀበልበት ዋነኛ መንገድ ንባብ መሆኑን ስናስታውስ የማንበብ ባህላችንን ዘመን የተሻገረ እና ረጅም እድሜ ያስቆጠረ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ያለው ትውልድ የንባብ ባህላችንን የዘነጋው እስከሚመስል ድረስ ለንባብ እየተሰጠው ያለው ትኩረት እየቀነሰ እንደመጣ በግልጽ እያየን ነው፡፡

ስለሆነም እንደዚ ያለ አነቃቂ መድረኮች በማዘጋጀት የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ቢሮው ጥረት ያደርጋል ብለዋል፤ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com