የጤፍ ነገር በካሊፎርኒያ

Views: 310

የአሜሪካ ተመራማሪዎች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ አማረጭ ምግብ ፍለጋ ላይ ናቸው ፡፡

በካፎርኒያ ጤፍን በመትከል እንደ አማራጭ ምግብ ለመተካት ተመራማሪዎች ጥናት እያደረጉ የነበረ ሲሆን አበረታች የሚባል ውጤቶች ማግኘታቸውም ታውቋል፡፡

በካሊፎርኒያ ለ40 ዓመታት ያህል በሩዝ እና በጥራጥሬ ዕሎች ላይ ጥናት ሲያደርግ የነበረው ኢትዮ -አሜሪካዊው ታሪኬ በርሄ ተስፋ በጤፍ ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየቱን ተናግሯል፡፡

ካሊፎርኒያ የአሜሪካ የምግብ ቅርጫ ብትሆን ለወደፊት ግን በዚሁ ትቀጥላለች ብሎ ማሰቡ ከባድ ነው ብሎ በመግለፅ ፤የአየር ንብረት ለውጥን በምክንያትነት አንስተዋል፡፡

ዴሬክ አዜቫዶ የተባሉት የ50 ዓመቱ አርሶ አደር ደግሞ ጤፍን በፈረንጆቹ 2018 ላይ በመትከል ውጤት እንዳዩበት ገልጸዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥም ለምርትነት የሚደርስ መሆኑን በመናገር አሁን ግን ጤፍን እየተጠቀሙበት ያለው ለምግብነት ሳይሆን እንስሳዎቻቸውን እየመገቡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪው ታረቀ በርኼ ጤፍ ተፈላጊነቱ ጨምሯ ቢሉም በአሜሪካ ብዙ ሰዎች እንጀራ የመመገብ ፍላጎታቸው አናሳ የሚባል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ዲህም አሜሪካውያን ከጤፍ ይልቅ ኩዊኗ የሚባል እህል ምርጫቸው አድርገዋል ሲል ሎስአንጀለስ ታይምስ ዘግቧል፡፡

ኩዊኗ፤ በደቡብ አሜሪካ ሀገራት ተመራጭ ምግብ ሲሆን የቦሊቪያ መንግስትም በሕገ-መንግስቱ ውስጥ “የምግብ ሉዓላዊነት” መብትን በማስፈር የአሜሪካ ተመራማሪዎች እህሉ በሌላ ቦታ እንዲበቅል ለማድረግ ያደረጉትን እቅስቃሴም ለመግታት ክስ መስርቶ እንደ ነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

ጥናቱ ጤፍ በካሊፎርኒያ በረሃማ አካባቢ መብቀሉ የጥናቱ ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com