የእስራኤል እና የኢትዮጵያ ስምምነት ለአፍሪቃም መልካም ዕድል ይዞ ሊመጣ ይችላል ተባለ

Views: 112

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በእስራኤል የሁለት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ በሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸው ላይ መክረዋል፡፡

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ፤በውይይታቸው እስራኤል የምታበረክተው አስተዋፅኦ መኖሩን ጠቁሟል፡፡

ኔታናሁም የኢትዮጵያ የንግድ መጠን 3 መቶ ሚሊዮን መድረሱን በመጠቆም የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነታችን መጠናከር ይኖርበታል ሲሉም አክለዋል፡፡

በደህንነት ጉዳይ ላይ ለመስራት ከስምምነት ደርሰው መፈራራመቸው ተሰምቷል፡፡

ከ30 ዓመት ወዲህም የሁለቱ አገራት ግንኙነት መሻሻል እንዳሳየ የተነገረ ሲሆን ኢትዮጵያ ለእስራኤል በፖለቲካው እና በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ አስፈላጊ መሆኗም ተጠቅሷል፡፡

እስራኤልም ለኢትዮጵያ ከቴክኖሊጂና ከጸጥታ ጉዳዮች ጋር በጋራ ለመስራት ጠቃሚ ሀገር ናት ተብሏል፡፡

እስራኤል ከአረብ አገራት በገባችው ጦርነት ሳቢያም የሁለቱ አገራት ግንኙነት ደካማ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ከዙህ ጋር በተያያዘም የአውግስታ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሚካኤል ቢሹኩ ሲናገሩም ከቀዝቃዘው ጦርነት በኋላ የሁለቱ አገራት ግንኙነት የተረጋጋ ቢሆንም ልዩ የሚባል ግን አይደለም ብለዋል፡፡

ግንኙነታቸው ልዩ እንዳይሆን ካደረጋቸው ነገር አንዱ ደግሞ የግብፅ ጉዳይ ነው፡፡

ግብፅ ከእስራኤል ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ሲኖራት ኢትዮጵያ እና ግብፅ ደግሞ በአባይ ወንዝ ዙሪያ ከስምምነት አለመድረሳቸውንም በምክንያትነት አብራርተዋል፡፡

ኔታናሁ በፈረንጆቹ 2016 አዲሰ የአፍሪካ ፖሊሲ በመንደፍ ‹‹ወደ አፍሪቃ መመለስ›› በሚለው ፖሊሲያቸው ከአገራቱ ጋር ሊሰሩ ቢሞክሩም ውጤታማ አልሆኑበት፡፡

ይህ የሁለቱ መሪዎች አዲሱ ስምምነት ምን እንደሆነ በስፋት ባይገፅም በንግድ፣በኢንቨስትምት እና በሌሎች ጉዳዮች በጋራ ለመስራት መስማታቸው ለሌሎች አፍሪቃ አገራትም ጥሩ ዕድል ሊሆን ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ግን ስጋት እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com