ኢትዮጵያ ፣ዛምቢያ እና ናይጄሪያን በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ዜጎቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ለማስቆም እየሰራን ነው አሉ፡፡

Views: 143

በደቡብ አፍሪካ በጆሃንስበርግ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌላ ሀገር ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ይገኛል ፡፡

በመሆኑም የዛምቢያ ፣ ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ዜጎቻቸውን ከጥቃት ለመከላከል ድርጊቱን በመቃው ላይ ይገኛሉ፡፡

ዛምቢያ ነገሩን ለመቃወም በሉሳካ በሚገኘው የደቡብ አፍሪቃ ኤምባሲ በመገኘት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለሀገሪቱ ፖሊስ የይፈቀድልን ጥያቄያቸውን አስገብተዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ ዓላማ ነገሩን በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም እና መፍትሔ ለማበጀት ሲሆን ምንም ዓይነት ጉዳት የሚያመጣም ሆነ አመፅ የሚያነሳሳ ነገር እንደማይካሄድ አፍሪካን ኒውስ በዘገባው ጠቁሟል፡፡

የኢትዮጰያ መንግስት በበኩሉ በደቡብ አፍሪቃ መረጋጋት እስኪመጣ ድረስ ዜጎች ውድ እና ያሸበረቁ ልብሶች እንዲሁም ጌጣጌጦችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ እና ሱቆቻቸውንም እንዲዘጉ ማሰሰቢያ ሰጥቷል፡፡

እንዲሁም ማንኛውም አጠራጣሪ እቅስቃሴ ቢመለከቱ ለፖሊስ አልያም በኤምባሲው ስልክ ቁጥር 012 346 42 57ወይም 012 346 29 47 በመደወል ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ ብሏል፡፡

ናይጄሪያ ደግሞ ደቡብ አፍሪቃን በንግድ ለመበቀል ቆርጣ መነሳቷን ገልፃለች፡፡

የአገሪቱ ዜጎችም መንግስት የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንዳለበት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ሲወተውቱ ነበር፡፡

በመሆኑም በናይጄሪያ የሚገኙ ግዙፍ ድርጅቶች እንደ
ኤምቲኤን፣ዲኤስቲቪ፣ ሾፕራይት እና ስታንቢክ ባንክ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏ ተሰምቷል፡፡

ድርጊቱ የናይጄሪያን ሰራተኞች እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚጎዳ ተነግሯል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com