ዜና

በደቡብ አፍሪካ ሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ

Views: 159

በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች በሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች ላይ ዘረፋ እና ግጭቶች በድጋሚ በመነሳቱ ምክንያት ሁለት ኢትዮጵያውያን ንብረታቸውን ከዘራፊዎች ለማትረፍ በመሄድ ላይ እያሉ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ከጆሀንስበርግ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ጁሊየስ በምትባል መንደር ያላቸውን የሱቅ ንብረት ለማትረፍ እየነዱ በነበረበት ወቅት የመኪና አደጋ ገጥሟቸው ህይወታቸው እንዳለፈ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ምክትል ሰብሳቢ ናህሊ ሙሳ ገልጸዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በውጭ አገር ዜጎች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ 81 ሰዎች የተያዙ ሲሆን፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ ባለው ሥፍራ ስምንት የከተማዋ አካባቢዎች ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው ሪፖርት ተደርጓል ሲል የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የፖሊስ ሚኒስተሩ ቤኪ ሴል እንዳሉት “ጥቃቱ ወንጀል ነው እንጂ ላሌ ነገር አይደልም” አብዛኛዎቹ ዘራፊዎች የመጡት ከጆሀንስበርግ ከተማ በቅርብ ከሚገኙት ዴንቨር እና ክሊቭላንድ መኖሪያዎች ነው ብለዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትላንት ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውና አደጋ ሊያደርሱ ከሚችሉ አጋጣሚዎች በመራቅ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com