የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በቀጣዩ ምርጫ አልሳተፍም አለ

Views: 106

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀውን የምርጫ ሕግ አስቸኳይ ማሻሻያ እንዲያደርግ የጠየቀ ሲሆን፣ አሁን ባለበት ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ግን በቀጣዩ ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የምርጫ ዓዋጅ በአስቸኳይ ተመልሶ እንዲታይም ጠይቋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል ከሆኑት 107 ፓርቲዎች ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከምርጫው በፊት ክለሳ ስለጠየቁ ወይም የምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ካጠረም ወደ ፊት እንዲገፋ መደረግ አለበት ሲሉ የጋራ አቋማቸውን አጋርተዋል፡፡

መንግሥት ዓዋጁን አሁን ባለበት መልኩ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ፣ የሚደረገው ምርጫ ተዓማኒነት የሌለውና ሀገሪቷንም ወደ ችግር እንድትገባ የሚዳርግ ይሆናል ተብሏል፡፡

ጉዳዪን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማትና ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲያዩትና ምላሽ እንዲሰጡበትም ምክር ቤቱ መጠየቁን ለማወቅ ተችሏል

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com