በሻሸመኔ እና በአዲስ አበባ ሰባት ሄክታር የካናቢስ ዕፅ እርሻ ወደመ

Views: 127

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ያሉ ከሰባት ሄክታር በላይ የካናቢስ ዕፅ እርሻን በተጠናቀቀው ዓመት እንዳከሰመ አስታወቀ፡፡

ከሰባት ሄክታር በላይ የካናቢስ ዕፅ እርሻ የወደመው በሻሸመኔ እና በመዲናችን አዲስ አበባ ነው ያሉት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ተቆጣጣሪ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መንግስተአብ በየነ ናቸው፡፡

ማነኛውንም አይነት አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም፣ ማዘዋወርም ሆነ ማሳደግ በኢትዮጵያ ሕገወጥ ተግባር ሲሆን፣ የካናቢስ ዕፅ ይዞ የተገኘ ሰው እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣም አቶ መንግስተአብ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ኮሚሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአደንዛዠ ዕፅ ዝውውር እጃቸው አለበት ያላቸውን የ17 አገራት ዜግነት ያላቸውን 80 ሰዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለም ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com