ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሟች ቤተ እስራኤላዊውን ቤተሰብ አነጋገሩ

Views: 121

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በእስራኤል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የቤተ እስራኤላዊውን የሟች ቤተሰሰብን አግኝተው አነጋገሩ፡፡
በያዝነወ ዓመት በእስራኤል ጋዛ የተገደለው አበራ መንግስቱ እና በፖሊስ መኮንን የተገደለው የ19 ዓመቱ ታዳጊ ሰለሞን ተካ መሞታቸውን ተከልሎ በእስራኤል አመፅ መነሳቱም አይዘነጋም፡፡
የቤተ እስራኤላውያን ሞት ለኢትዮጵያና እስራኤል ሀዘን እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ተናግረዋል፡፡
ይህንን አስመልክቶም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአበራ እናት ጋር መነጋገራቸው እና ለሰለሞን ቤተሰቦችም መልዕክት መላካቸው ‹‹ዘ ጄሩሳሌም ፖስት›› ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥላጣን ከወጡ በኋላ፣ ወደ እስራኤል ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ጊዜያቸው ነው ብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በእስራኤል የሁለት ቀን ጉብኝታቸው ከእስራኤሉ አቻቸው ቤኒያሚን ኔታናሁ ጋር በኢንቨስትመንት፣ በጸጥታ፣ በንግድ፣ በግብርና እና በሌሎች ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡
የእስራኤላ በለሃበቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በግሉ ዘርፍ በጤና፣ በቴሌኮም በኃይል አቅርቦት፣ በኢንኖቬሽን እና በሎጂስቲክ በመሰማራት መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሀገረ እስራኤል የቤተ እሰራላውያን ቁጥር 150 ሺህ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com