እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ከደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለመስራት ፍላጎት እንዳለት ገለጸች

Views: 130

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በደህንነት ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር በጥምረት ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናገሩ፡፡
ይህንን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በእስራኤል ባደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አስመልክቶ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
እኛም በደህነነት ላይ በቂ ልምድ ያለን በመሆኑ፣ ያለንን ልምድ በማጋራት እና በማቅረብ በጋራ መስራት እንችላለን ሲሉ ኔታንየያሁ ለኢትዮጵያው አቻቸው ተናግረዋል፡፡
በአፍሪቃ ቀንድ ካሉ አገራት መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸው ሲሉም ኔታንያሁ ተናግረዋል፡፡
በ1960ዎቹ ጥቂት የአፍሪቃ አገራት፤ እስራኤል ከጎረቡቶቿ የዐረብ አገራት ጋር በነበረችበት ጦርነት እንዲሁም በደቡብ አፍሪቃው የአፓርታይድ ሥርዓት እጇ አለበት በማለት አገራቱ ለመስራት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪቃ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ መሆኗን እና አሁንም ቢሆን ከድህነት ያልተላቀቀች ሀገር ናት ያሉት ኔታናሁ፤ በኢንቨስትመንት፣ በ‹‹ኢኖቬሽን›› እና በደህነንት ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት መነጋገራቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በእስራኤል 150 ሺህ ቤተ እስራኤላውያን ሲኖሩ፣ 50 ሺህ የሚሆኑት ዜጎች በአስራኤል የተወለዱ ናቸው ብሏል- ዘገባው፡፡
በፈረንጆቹ 2016 ላይ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com