‹‹ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለች ዝም የምንልበት ምክንያት የለም›› ሲሉ የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተናገሩ

Views: 198

ከዚህ ቀደም በጅግጅጋ እና በሀዋሳ አካባቢ አብያተ-ክርስትያናት ተቃጥለዋል፤ አሁን ግን ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል ዝም የምንልበት ጉዳይ አይሆንም ሲሉ የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ገለጹ፡፡
ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ልዕልና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማቃጠል ድፍረትና ተንኮል ነው ሲሉ ብጹእነታቸው ተናግረዋል፡፡
መንግስትም ቢሆን ቤተ ክርቲያኒቱን ሊጠብቅ ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን የሚሆነው ነገር ከባድ ሀገራዊ ክስረት ነው የሚያስከትለው ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸዋል፡፡
እስከ አሁን ቤተክርስቲያኒቱ ጥቃት ሲፈጸምባት ነገሩን ለማጣራት ዝምታን መርጣ ነበር ያሉት አቡነ መቃርዮስ፤ ድርጊቱን ለማውገዝ መፍጠን ነበረባት በማለት ተናግረዋል፡፡
በሶማሌ ክልል አሁን ያለው ሁኔታ በተመለከተም ክልሉ ሰላማዊ መሆኑን፤ ስጋት የሚባል ነገር እንደሌለ በመግለፅ የክልሉ መንግስትም በጸጥታ ዙሪያ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከዓመት በፊት በሶማሌ ክልል አብያተ ክርስቲያናትን ያቃጠሉ፣ እናቶች እና ወጣቶችን የደፈሩት እንዲሁም የገደሉ ወንጀለኞች ጉዳያቸው በሕግ እንደተያዘ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ለኢትዮ-ኦንላይን አሳውቀዋል፡፡
በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ለተፈጸመባት ጥቃት መንግስትም ቢሆን ካሳ መክፈል እንዳለበትም አቡኑ አሳስበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com