‹‹የፖለቲካ እስረኛ ፍየሎች›› እንዲፈቱ ተጠየ

Views: 199

 የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኘው ፓለቲከኛ፤ ዜናዊ አስመላሽ ፍየሎቹ እንደታሰሩበት አሳወቀ፡፡
የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለፍትሕ (ዓረና) ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ፣ ስለጉዳዩ ሲናገሩም ፍየሎቹ የታገዱበት አቶ ዜናዊ አስመላሽ ከፖለቲካው እንዲወጣ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ዜናዊ አስመላሽ አሥራ ስድስት ፍየሎች የተወሰዱበት ከመኖሪያ ቤቱ አከባቢ ሲሆን፣ እሮብ ቀን በአከባቢ የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት መወሰዳቸውንም አብራርተዋል፡፡
አቶ ዜናዊ ከዚህ ቀደም በገዢው ፓርቲ ህወሓት ማስፈራራት እንደደረሰባቸው እና መታሰራቸውም ተነግሯል፡፡
የታሰሩባቸው ፍየሎች እንዲለቀቁላቸው ጉዳዩንም ለፖሊስ ማመልከታቸውን አሳውቀዋል፡፡
በአሁን ሰዓት ሶስቱ ፍየሎች ከእስር ያመለጡ ሲሆን፣ ቀሪ 13 ፍየሎች ደግሞ አሁንም በእስር ላይ ናቸው ተበሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለፍትሕ ፓርቲ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ ተቃዋሚ ፓርቲ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት ለሚደረገው ምርጫም አባላቱን እያደራጀ እና እያንቀሳቀሰም ይገኛል፡፡
አቶ አብረሀ ደስታ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ‹‹ህወሓት ከሰዎች አልፎ ወደ ንፁህ እንስሳት ዞሯል›› ሲሉ ያሰፈሩ ሲሆን፣ ይህ ንግግራቸውም በተለያዩ ሚዲያዎች አነጋጋሪ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ንግግራቸው ነቀፌታ ቢኖረበትም፣ በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ደግሞ ለእንስሳት ተቆርቋርዎች የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወስዱ ብሎም ‹‹የፖለቲካ እስረኛ ፍየሎች›› ይለቀቁ የሚል ዘመቻም እንዲከፈት አድርጓል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com