ደኢህዴን ርዕሰ መስተዳደሩን መረጠ

Views: 248

አቶ እርስቱ ይርዳው ማናቸው?

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) አቶ እርስቱ ይርዳውን ርዕሰ-መስተዳድር በማድረግ የሾመ ሲሆን፣ የቀድሞውን ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስን በመተካት ክልሉን በምክትል ፕሬዚዳንትነት የሚመሩ ይሆናል ተብሏል፡፡
ለመሆኑ አቶ እርስቱ ይርዳው ማናቸው? ከዚህ ቀደምስ የነበራቸው የሥራ ልምድ ምን ይመስል? የሚለው ጉዳይ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
የትምህርት ዝግጅት
በማኔጅመነት የመጀመሪያ ዲግሪ
ሁለተኛ ድግሪያቸውን በከተማ ልማት አስተዳደር ከሲቪል ሰርቪሰ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል
የሥራ ኃላፊነታቸው ምን ይመስላል ?
ከ1985 ዓ.ም እስከ 2001 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ከወረዳ አመራርነት እስከ ዞን አስተዳዳሪነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ከ2002 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 25 ቀን2011 ዓ.ም ደግሞ በአዲሰ አበበ ከተማ አስተዳደር እና በፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግለዋል እነርሱም፡-

በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የክልል ጉዳዮች አማካሪ በመሆን
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዴኤታ
በግብርና ሚንስቴር የታዳጊ ክልሎች ልዩ ድጋፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ እና የንግድ ቢሮ ኃላፊ፤
የኢፌድሪ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር በመሆን
የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ከሚሽነር በመሆን እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም እየሰሩ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀጣዩ የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር በመሆን ተሹመዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com