ጉዳዩ ወደ መጨረሻ ሂደቱ ደርሷል

Views: 151

በሰኔ 16ቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የድጋፍ ሰልፍ የቦምብ ጥቃት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች በፍጥነት ፍርድ እንዲወሰንባቸው እየሰራን ነው ሲል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

የዛሬ ዓመት ሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የድጋፍ ሰልፍ ላይ በወጡ ንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ ቤትም ሆነ በጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኩል አስፈላጊውን በቂ ማስረጃ በማቅረብ በፍጥነት ብይን እንዲያገኝ እየተሰራበት እንደሆነ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱሉ ለኢትዮ ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ እንዲያገኝ አሁን ወደ መጨረሻ ሂደቱ ላይ ደርሰናል ያሉት አቶ ዝናቡ አቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል ፍርድ ቤቱ ደግሞ ተጠርጣሪዎቹ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ብይን ሰጥቷል፡፡ “ከነዚህ የተወሰኑ ሂደቶች በኋላ ጉዳዩ በእርግጠኝነት የፍርድ ውሳኔ የሚያገኝበት ሁኔታ ነው የሚኖረው” ብለዋል፡፡

በሽብር ጥቃቱ እጃቸው አለበት የተባሉ በርካታ ተጠርጣሪዎች በጊዜው ተይዘው ሰፊ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

“የፍርዱ ሂደት ዘግየ እያሉ የሚጠይቁ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ እናውቃለን፤ በእርግጥ ለተጠርጣሪዎቹ ፍርድ የማሳለፉ ጉዳይ የፍርድ ቤቱ ቢሆንም መዘግየቱ እውነት ነው” ሲሉ አቶ ዝናቡ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በቦምቡ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች መንግስት በግዜው ካደረገልን የህክምና ድጋፍ ውጪ በአካላችን ላይ ጉዳት ስለደረሰብን እንደ በፊቱ ተሯሩጠን መስራት የማንችልበት ሁኔታ ስላለን በዘላቂነት ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ ቅሬታቸውን ለኢትዮ ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

በዓመቱ ሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ትፈለጋላቹ ተብለን የተጠራን ቢሆንም በወቅቱ በአማራ ክልል በተከሰተው የባለስልጣኖች ግድያ ምክንያት እንዳትመጡ ተብለና ብለዋል፡፡

በጥቃቱ እጃችን፤ እግራችን፤ አይናችን እና የተለያዩ የአካል ክፍሎቻችንን የተጎዳን ሰዎች አለን፡፡ በዚህም ጉዳት የተነሳ የዕለት ገቢያችንን ሰርተን ማግኘት ስላልቻልን መንግስት ሊደግፈን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com