7ተኛው የበጎ ሠው ሽልማት አሸናፊዎች ታወቁ::

Views: 562

የ2011ዓ.ም 7ተኛው የበጎ ሠው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በኢንተር ከንትኔንታል የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ስህለወርቅ ዘውዴን ጭምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፉዎች እና ጥሪ የተደረጋላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል።

በሥነ ሥርዓቱ ለይ በቅርሥና ባህል ዘርፍ የ2011 ዓ.ም አሸናፊ አቶ አብድልፈታህ አብደላ ተሸላሚ ሆነዋል::

በሳይንስ ዘርፍ ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው የ7ተኛው የበጎ ሠው ሽልማትን አግኝተዋል::

ሌላው በመንግሥታዊ የስራ ተቋማት ኃላፊነት ዘርፍ ተሸላሚ የሆኑት አቶ ግርማ ወንዳፍራሽ ናቸው::

በንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ደግሞ አቶ ነጋ ቦንገር የዓመቱ በጎ ሠው ተብለው ሽልማትን አግኝተዋል::

ዶ/ር አብዱልአዚዝ ኢብራሂም በበጎ አድራጎት (እርዳታ እና ሰብአዊ መብት) የዓመቱ በጎ ሠው ተብለዋል::

በኪነ ጥበብ/ ሥነ ጥበበብ ፣ፎቶግራፍ / ዘርፍ አቶ በዛብህ አብተው ተሸላሚ ሆነዋል::

እንዲሁም በሚዲያ እና ጋዜጠኝነት ዘርፍ የ7ተኛው የ2011ዓ.ም የዓመቱ በጎ ሠው በመባል የተሸለሙት አቶ አማረ አርጋዊ ናቸው።

በዳያስፖራዎች ዘርፍ የሠብአዊ መብት ተሟጋች አቶ ኦባንግ ሜቶ ተሸላሚ ሢሆን የጋሞ ሽማግሌዎች ደግሞ የ7ተኛው የበጎ ሠው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com