በቢሾፍቱ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የውሃ ፓርክ ተመረቀ

Views: 97

በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነና በ72 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የውሃ ፓርክ በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሪዞርት ተመርቆ ለህዝብ ክፍት ሆነ፡፡

የውሃ ፓርኩ የመዝናኛ ስፍራዎች፤ የባህላዊ ምግብ አዳራሾች እና ከ100 በላይ ሱቆች በውስጡ አካቷል ተብሏል፡፡

ፓርኩ በከፍተኛ ወጪ የተሰራና እና በአንድ ጊዜ ከ1900 በላይ ሰዎች የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን ለኢትጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን መዝናኛ እንደሚሆን ተጠቁሟል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡

ግንባታውን ለማጠናቀቅ 2 ዓመት ከ6 ወር እንደፈጀም ተገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com