ቶሺባ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ ግብዣ ቀረበለት

Views: 109

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቶሺባ ኢነርጂ ሲስትም ሶሉሽን ኮፕሬሽንን በጎበኙበት ወቅት ድርጅቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ ግብዣ አድርገዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ኮፕሬሽኑ የእንፋሎት ተርባይኖች ማምረቻ ቦታን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስጎበኛቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በቲውተር ገፁ አሳውቋል፡፡
ቶሺባ ኮፕሬሽን በኢትዮጵያ በተለይም በጂኦተርማል ሀይል ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ግብዣ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ኮሪያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጨርሰው በጃፓን ዮኮሃማ ከተማ በሚካሄደው ሰባተኛው የጃፓን እና የአፍሪካ ሀገራት የልማት ጉባኤ ላይም እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com