ዜና

በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለአስር ዓመታት ያስቀጣል

Views: 212

ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን የሚከላከል ረቂቅ ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ አዋጅ አስታውቋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ መሰረትም ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውር የተገኘ አካል እስከ አስር ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሊቀጣ ይችላል ነው የተባለው፡፡

በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር ወንጀል ዙሪያ የመቅጫ ግጎች ቢኖሩም በጦር መሳሪያ አያያዝ፣ቁጥጥርና አስተዳድር ዙሪያ በዝርዝር የተቀመጠ ሕግ አለመኖሩን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡ በወንጀለኞች ላይ ይጥሉት የነበረው የቅጣት መጠንም አነስተኛ እንደነበር ጠቁሟል፡፡

አዋጁ የጦር መሳሪያ መያዝ የሚፈቀድላቸውን እና የሚከለከሉ ግለሰቦችን እና ተቋማትን የሚለይ ነው፡፡ የሚይዙትን የጦር መሳሪያ ዓይነትም ይደነግጋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ 21 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሕጋዊ የጦር መሳሪያ እንዲይዙ ተፈቅዷል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ፀድቆ ወደ ሥራ ሲገባ በባለቤትነት ሰላም ሚንስቴር እንደሚያስተዳድረውም ታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com