ባለፈው በጀት ዓመት ከግብርና የውጭ ገበያ 318 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

Views: 285

ኢትዮጵያ ካለፈው የ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት ወደ ውጭ ገበያ ከተላከው ከግብርና ምርት 318 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በበጀት ዓመቱ 261 ሚሊዮን ዶላሩ ከአበባ ምርት ብቻ የተገኘ ሲሆን ቀሪው 57 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከአትክልት፣ፍራፍሬ እና ሌሎች ዕፅዋት ምርቶች የተገኘ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኃይሉ እንደገለፁት ዘርፉ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ከማስገኘት አንፃር እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

ከመቶ በላይ ኩባንያዎች በአበባ፣በፍራፍሬና በዕፅ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ መሆኑን አቶ መኮንን ገለፀዋል፡፡ የገበያ ፍላጎቱን ለማሟላትም ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶቿን ወደ ኔዘርላንድ፣ሳውዲ አረቢያ፣ብሪታኒያ፣አሜሪካ፣ጃፓን፣ኖርዌይ፣ጀርመን፣የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ቤልጄም እና ጣሊያን እየላከች ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com