የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በእርጥበት ምክንያት ተስተጓጎለ

Views: 153

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የአዲስ አበባ ማኮብኮቢያው ላይ ውሃ በመቋጠሩ ከትናንት በስቲያ ሰኞ፤ ነሐሴ 19 ቀን በሰላም ማረፍ አለመቻሉ ታውቋል፡፡ ይህ እንግዳ ክስተት በመፈጠሩም አቅጣጫውን ቀይሮ አርፏል፡፡ አውሮፕላኑ የበረራ ቁጥር 307 ኢትዮጵያ ሲሆን በችግሩ ምክንያት ጉዳት አልደረሰበትም፡፡

አውሮፕላኑ ከኬንያ፤ናይሮቢ ተነስቶ አዲስ አበባ የደረሰ ሲሆን አኮብኩቦ የሚያርፍበት ቦታ በእርጥበት በመሞላቱ ነው አቅጣጫውን ቀይሮ ያረፈው፡፡

የበረራ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት አውሮፕላኑ ሲደርስ ፍጥነቱ ኖት በተሰኘው አሐድ ተለክቷል፡፡ ይኸውም በ155 ኖት ፍጥነት ማረፉን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ይህን መሰሉ የማኮብኮቢያ ቦታ መዘጋት ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስቶ ባሕር ዳር ለማረፍ የሞከረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ተከስቷል፡፡ በወቅቱ የአውሮፕላኑ ማኮብኮቢያ ላይ መኪና የገባበት ሲሆን ለማረፍ ዝቅ ብሎ የነበረው አውሮፕላን እንደገና ከፍታውን ወደ ላይ በመጨመር ከተማዋን ሲዞር ከቆየ በኋላ በሰላም ለማረፍ ችሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com