ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ጃፓን ገቡ

Views: 126

ጠቅላይ ሚንስትሩ በደቡብ ኮሪያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ጃፓን ገብተዋል፡፡ ጃፓን ውስጥ በዮኮሃማ ከተማ በሚካሄደው ሰባተኛው የጃፓን እና የአፍሪካ ሀገራት የልማት ጉባዔ ላይም እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

ከጉባዔው በተጓዳኝ ከጃፓን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩም ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጉባዔው ቀደም ብሎ በጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ጃፓንን እንዲጎበኙ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ጉባዔውን በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com