ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚያገናኘው የየብስ መንገድ በመጭው መስከረም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

Views: 176

መንገዱ ግንባታው ተጠናቆ መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም ይመረቃል፡፡ ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተጀመረው በኤርትራ የሀገር መከላከያ ኃይል የሚገነባው ይህ የ90 ኪሎ ሜትር መንግድ በአሁኑ ወቅት ዘጠና በመቶ መጠናቀቁን ኤሪትራን ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ቀሪው አስር በመቶም በመጭዎቹ ሁለት ሳምንታት ይጠናቀቃል ብሏል ዘገባው፡፡

መንገዱ ቀደም ሲል በስድስት ሜትር ስፋት የተሠራ ሲሆን አሁን በተደረገው ማሻሻያና ተጨማሪ ግንባታ ሃያ አምስት አዳዲስ ድልድዮች ተገንብተውለታል፡፡

በመንገዱ ግንባታ ላይ ከኤርትራ የሀገር መከላከያ በተጨማሪ አምስት የኤርትር የመንግድ ግንባታ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com