ኢትዮጵያ ጳጉሜን በበጀት ቀመሯ ባለማካተቷ በየዓመቱ 54 ቢሊዮን ብር እያጣች ነው

Views: 1237

በጳጉሜ ወር የገንዘብ ዝውውር ቢኖርም ወሩ በበጀት ቀመሩ ግን አለመካተቱ ሀገራዊ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑን የዘርፉ ተመራማሪ ተናገሩ፡፡ ጳጉሜ ስድት በሚል መፅሐፋቸው የሚታወቁት በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ኃብት አስተማሪው ፋሲል ጣሰው እንደገለፁት ጳጉሜ በበጀት ቀመሩ ባለመካተቱ ሀገሪቱ ልታገኝ የሚገባትን 54 ቢሊዮን ብር እያጣች ነው፡፡

ከአምስት እስከ ስድስት ቀናት ያለው ጳጉሜ በ2012ቱ በጀት ዓመት ውስጥ ቢካተት ኖሮ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ በበጀት ዓመቱ ተካቶ ሥራ ላይ ይውል ነበር፡፡

በዚህ ወር ሰራተኞች ደሞዝ አይከፈላቸውም፣አከራዮች ኪራይ አይከፈላቸውም፣መንግሥትም ግብር አይከፈለውም፡፡ ይህም ሀገሪቱን ለኪሳራ ዳርጓል ነው የተባለው፡፡ የንብረት ባለቤትነት መብትንም የሚጣረስ ነው፡፡

ሰራተኞች በጳጉሜ ያለደሞዝ በመሥራታቸው ወርሃዊ የገንዘብ ድልድላቸው እስከ ጥር ድረስ እንደሚጣረስም ተመራማሪው ገልፀዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com