ለአንድ ዓመት በፖሊስ ሲፈለጉ የቆዩት የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ታሰሩ

Views: 30

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።

ተከሳሹ ከሰኔ 05 እስከ 12 ቀን 2010 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የወላይታና ሲዳማ ብሔሮችን በማጋጨት ለሰው ሕይወት መጠፋት እና ንብረት መውደም መከሰሳቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ በተለይ ለኢትዮ ኦን ላይን ገልፀዋል። አቶ ቴዎድሮስ ገቢሳ የእርስ በእርስ ግጭት በማነሳሳትም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከሰዋል።
ፌዴራል ፖሊስ ተከሳሹን ትናንት ነሀሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ሲሆን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆሳዕና 13ኛ ተዘዋዋሪ የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com