የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

Views: 193

በአዲስ አበባ ከተማ በ18 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል በኳታር መንግስት ሊገነባ ነው፡፡

የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ከኳታር የልማት ፈንድ ፕሮጀክት ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ሆስፒታሉን የማስገንባት ሂደት በፍጥነት ስራውን ለማስጀመር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡

የሆስፒታሉ ግንባታ ሁለት ምዕራፎች የሚኖሩት ሲሆን ፤ የመጀመሪያ ምዕራፍ የህንፃ ግንባታውንና  ባለሙያዎችን ስልጠና የሚያካትት ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ልዑክ ቡድኑ ከኳታር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከተለያዩ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በዘርፉ ትብብር ለማድረግ እንዲቻል የጎንዮሽ ውይይት ማድረጉን በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com