“ደብረፅዮን” የሚባለው ልብስ ተፈላጊ ሆኗል እየተባለ ነው

Views: 220

ፖለቲካን በፈገግታ!

በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል፣ በአማራ ክልል በሰቆጣና በላሊበላ ደግሞ ሻደይ፤ አሸንድዬ እና ሶለል በሚል ስያሜ፣ ከነሐሴ 14 ቀን ጀምሮ፤ በተለይ በሴቶች የሚከበረው ይህ ዓመታዊ በዓል ሴቶች የተለያዩ አልባሳትና ጌጣጌጦችን በማድረግ በባህላዊ ጭፈራዎች ደምቀው የሚታዩበት ነው፡፡

በዘንድሮ ክብረ በዓል የተለያዩ አዳዲስ ልብሶች ዲዛይን የሚታይበት እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን፣ በተለይም በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት እየጋለ የመጣውን የፖለቲካ ጉዳይ የሚያንፀባርቅ በሚመስል መልኩ አልባሳት በትግራይ ክልል ባለስልጣናት ተሰይመዋል ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡

ከአልባሳቱ መካከል በክልሉ ርዕሰ መሥተዳደር ‹‹ደብረፅዮን›› የተሰኘው ልብስ ዋነኛ ተፈላጊ ሲሆን፣ ሸማቾችም የትኛው ነው ደብረፅዮን የሚባለው ልብስ በማለት በብዛት እንደሚሸምቱት የልብስ ስፌት ባለሙያ የሆኑት አቶ የማነ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ይህ የልብስ አይነት በትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማ ያሸበረቀ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ከነዚህ በተጨማሪም፣ በቀድሞው የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ጌታቸው አሰፋ፤ በቅርቡ ህይወታቸው በጠፋው የፌዴራል መከላከያ ሚንስቴር ኢታማዦር ሹም ሰዓረ መኮንን፤ የክልሉ ባለሥልጣን አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የሚባሉ አልባሳትም በገበያው ላይ በስፋት እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com