ከመጪው ዓመት ጀምሮ የአስረኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደማይኖር ተገለፀ

Views: 948

በአዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ መሠረት፣ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የአስረኛ ክፍል አጠቃላይ መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀር እና ተማሪዎች ስድስተኛ ክፍል ሲደርሱ ክልላዊ ፈተና እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌጤ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት በክልሎች ይሰጥ የነበረው የ8ተኛ ክፍል ፈተና፣ በአዲሱ ፍኖተ-ካርታ መሠረት ሀገር አቀፍ እንደሚሆን እና በቀደሙት ዓመታት የ6ተኛ ክፍል ፈተና ይሰጥ እንደነበረው ሁሉ ከሚቀጥለው ዓመት በኋላ ለ6ተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ በሚደረገው የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት አወቃቀር ላይ በሚደረገው ለውጥ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ፤ ከ7ኛ -8ኛ ክፍል መለስተኛ እንዲሁም ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም፣ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ እንዳሉት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና መግባት የሚፈልጉ ተማሪዎች 12ተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እንደሚጀምሩም ጠቁመሟል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com