‹‹እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገራት የሴቶች ጥቃት አልቆመም››

Views: 147
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት አሁንም በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት እንዳልቀነሰ IRC ገለጸ፤ በሥሩ የምትሰራውን ኢፍራህ-ን ደግሞ ዋቢ ምስክር አድርጎ አቅርቧል፡፡
The International Rescue Committee (IRC) በተሰኘው ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅት ውስጥ የምትሰራው ኢፍራህ፣ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም እየሰራች ትገኛለች፤ በዚህም ብዙ ተሞክሮ አላት፡፡
በመጀመሪያ ገና ሥራዬን ስጀምር፣ በአካባቢ ማሕበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው እና የማሕበረሰቡ መሪዎች ገና ወጣት በመሆኔ፣ እኔን ሊሰሙኝ አይፈልጉም ነበር ስትል የምትገልጸው ኢፍራህ፣ 27 ዓመት ቢሆናትም፣ በማኅበረሰቡ መሪዎች ግን ልክ እንደ ልጅ እንደምትታሰብ ገልጻለች፡፡
ኢፍራ ሴቶችን ጥቃት እንዳይደርስባቸው የመከለከል ሥራዋን መስራት ስትጀምርም፣ በአካባቢው ሕብረተሰብ መገለል ደርሶባት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡
አሁን ግን የአካባቢው መሪዎች ጓደኞቼ ናቸው ስትል በፈገግታም ታብራራለች፡፡  
ሴቶችን እና ልጃገረዶች ላይ ለመስራት ፍላጎቴ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ወደ ሥራ የምታመራው ማለዳ 12 ሰዓት በመነሳት ሲሆን፣ አንድ ሰዓት ላይ ደግሞ ቢሮ ትገኛለች፡፡
ሁለት ሰዓት ደግሞ ኢፍራህ ኃሎዋይን በተባለ የሥደተኞች መጠለያ ካምፕ ትደርሳለች፤ ካምፑም በአየርላንድ ግብረ ሠናይ ደርጅት ድጋፍ ይደረግለታል፡፡
የእኔ ሥራ ብዙ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ከሚደርስባቸው ጥቃት ተላቀው የወደፊት ሕይወታቸውን እንዴት መምራት እንዳለባቸው እና ማሕበራዊ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር የግንኙነት መረብ በማዘጋጀት አንዱ አንዱን የሚረዳበት መንገድ ማዘጋጀት ነው ብላለች፡፡
ከ50 ሺህ በላይ ስደተኞች በካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ብዙዎችም በሶማሊያ አካባቢ በነበረው ግጭት እና ድርቅ ሳቢያ ነው ወደ መጠለያ የገቡት፡፡
ይሁን እንጂ፣ አሁንም በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መቀጠሉን እና በተለይም የቤት ውስጥ ጥቃት እንዳልቆመም ትናገራለች- ኢፍራህ፡፡
ሴቶቹ በባላቸው ተደብድበው ወደ ማዕከላችን ይመጣሉ፤ ይህንን ደግሞ እኔ ምስክር ሆኜ የተመለከትኩት ጉዳይ በመሆኑ ደፍሬ  መናገር እችላለሁ፡፡
ቢሆንም ግን፣ አሁን ያለው ነገር ለእኔም ሆነ ለልጆቼ የወደፊቱ ሕይወት ተስፋን የሚሰጥ ነው ብላለች፡፡
ባለፉት ሶስት እና አራት ዓመታት ውስጥ የወንዶች አመለካከት ላይ መሻሻል ታይቷል፤ አሁን ቢሆን ግን የሚቀር ነገር አለ ትላለች፡፡
አንዳንድ ወንዶች፤ ሚስቶቻቸው ወደ ማዕከሉ መሄዳቸውን እንደማይወዱ እሰማለሁ፤ ስለሆነም ሴቶች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ የመከላከሉን ሥራ ከወንዶቹ ጋር በጋራ በመሆን በኃለፊነት መስራት አለብን ስትልም ታስረዳለች፡፡
በካምፕ ውስጥ ያሉት ሴቶች የሥራ ዕድል አጋጣሚ እንኳን የላቸውም ይህ ሌላ ፈተና ነው ብላ የምታስረዳው ኢፍራህ፤ ድጋፍ እና ሥልጠና መስጠት ክህሎት ከሌለ፣ ገንዘብ እንኳን ማግኘት ከባድ እንደሆነ፣ ይህ ደግሞ ቤተሰብን ለመርዳት ከባድ ነው ስትል ኢህራህ ታብራራለች፡፡
የ30 ዓመቷ ማርያም፤ በኢፈራህ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ሴቶች መካከል አንደኛዋ ናት፤ እሷ ስትናገርም እኔ ባለፈው ዓመት ነበር በጎረቤቴ ጥቃት ተፈጽሞብኝ ወደ ማዕከሉ የመጣሁት፡፡
ጎረቤቴ ሴት ልጄ ላይ ጥቃት ሊፈፅምባት ሲል፣ እሷን ለመከላከል ስል በሁለታችንም ላይ አካላዊ ጥቃት ፈፅሞብናል ብላለች፡፡
ምሽቱንም በለቅሶ እና በሀዘን ነበር ያሰለፍነው ስትል በማስታወስ፣ ያኔ ኢፍራህም ጥሩ ድጋፍ አድርጋልናለች፤ የወደፊት ሕይወታችንንም በተስፋ እንድንመለከት አድርጋናለች ስትል አስረድታለች፡፡
አሁንም ማርያም ማስረዳቷን ቀጥላለች፤ ልጆቼ እንዲማሩ እና ውጤታማ ሆነው ማየት እፈልጋለሁ፤  ስለዚህ ደግሞ ኢፍራህ እኛ ሴቶችን እያበረታታችን ነው ብላለች፡፡
ኢፍራህ-ም በቡኩሏ፣ አንድ ግለሰብ የ14 ዓመት ታዳጊን ደፍሮ፣ ታዳጊዋ ፍትህ እንድታገኝ እና እስራት እንዲፈጸምበት የራሴን ደርሻ በመወጣቴ፣ ከእኔ ትልቁ እና ካስደሰቱኝ ስራዎች አንዱ ነው ብላ ታስታውሳለች፡፡
የተደፈረቸውም ታዳጊ ወደ እኛ ለመጀመሪያ ጊዜ በመምጣት የጤና እና ሕጋዊ ድጋፍ እንድታገኝ አድርገናል፤ ፍትህ በማግኘቷም እጅግ ደስ ብሎኛል፡፡
ይህ የማይታመን ስራ ነው፤ በስራዬ እርካታ ተሰምቶኛል የምትለው ኢፍራህ፣ ሥራን ከቤተሰቧ ተለይታ እየሰራች እንደሆነም ገልጻለች፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com