ቡሄ በሉ ፻ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዛሬ ይከወናል

Views: 223

‹‹ዱላችን ለጭፈራችን፤ ጭፈራችን ለሠላማችን›› በሚል መሪ-ቃል በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ዛሬ ምሽት የጥበብና የባሕል መርሃ-ግብር እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ለኢትዮ-ኦንላይን አስታወቁ፡፡

ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ የሚከናወነው የኪነጥበብ ምሽት፣ በአጠቃላይ የቡሄ በዓል ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

በዕለቱም ለቡሄ በዓል አከባበር አስተዋፅኦ ላደረገ ተቋም ሽልማት እንደሚደረግም የሀብል መልቲሚዲያ እና ማስታወቂያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚኪያስ ጌታቸው ገልጿል፡፡

በዕለቱም ቅኔ፣ ግጥም፣ ዲስኩር እና ሙሉ በመሉ የቡሄ በዓል አከባበር ላይ የሚያተኩር ዝግጅት እንደሚከወን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በምሽቱም አንጋፋ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች መካከል የኢትዮጵያ የጃዝ ሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄ በክብር እንግድነት የሚገኝ ሲሆን፣ አንጋፋው ገጣሚ ነብይ መኮንን እና ሌሎች ገጣሚያን እና የጥበብ ሰዎች በመድረኩ ላይ በመገኘት ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉም ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com