ንሥረ-ኢትዮጵያ ወደ ጆን ኤፍ ኬኔደ አመራ!

Views: 177

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጆን ኤፍ ኬኔዲ አየር መንገድ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ለሶስት ቀናት ወደ ጆንኦፍ ኬኔዲ አየር መንገድ በረራ ጀመረ፡፡

በአፍሪካ ካሉ አየር መንገዶች ውስጥ በውጤታማነት፣ በአገልግሎት ሰጪነት ተቀባይ እንዲሁም ቀዳሚው የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በሳምንት ሦስት ቀን ወደ ኒዮርክ ጆኖፍ ኬኔዲ አየር መንገድ  በረራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የጆኖፍ ኬኔዲ አየር መንገድ  በጣም ሥራ ከሚበዛባቸው ከዓለም አቀፍ የሰሜን አሜሪካ አየር መንገዶች ውስጥ ስድስተኛ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ‹‹አየር መንገዱ በረራውን ጀምሯል ብዬ ሳበስር ደስታ ይሰማኛል፤ ይህም በኒዎርክ ከተማ ሁለተኛው መዳረሻችን መሆኑ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ባላት የንግድ እና ሌሎች ዘረፈ-ብዙ ግንኙነቶች በረራውን መጀመራችን በአገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ይረዳል ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

አዲሱን በረራ ጨምሮ አየር መንገዱ በሳምት 24 በረራዎችን በሰሜን አሜሪካ እና አፍሪካ መካከል ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም፣ በአፍሪካ እና በአሜሪካ መካከል የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት እና የሰዎች ለሰዎች ግንኙነትን ለማጠናከርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com