ዜና

ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ በአንድ ሊቆሙ ነው

Views: 298

ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ ደህንነትናን መከላከያን ጨምሮ አባል በሆኑባቸው ዓለማቀፋዊ እና ክልላዊ መድረኮች በመቀራረብ እና ተመሳሳይ አቋም በማራመድ ለመሥራት ከሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ምንጮች ለኢትዮ-ኦንላይን አስታወቁ፡፡

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የዜና ምንጮቻችን፣ ሁለቱ አገራት የደህንነትና የመከላከያ ትብብር ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፤ ቀደም ሲል ጀምሮ በቀጠናዊ፣ ክልላዊ እና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የሚያራምዱትን ተመሳሳይ አቋም ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በ3ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብስባ ላይ ለመካፈል ወደ ዑጋንዳ ካምፓላ ከተማ ከአቀናው በውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ጋር ያመሩት የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ፣ ከደህንነትና ከመከላከያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ስምምነቶች አድርገው ተመልሰዋል፡፡

እነዚህን የትብብር ዘርፎች ለመተግበር የሚያስችል የሚንስትሮች የጋራ ኮሚሽን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ተፈራርመው ወደ ሥራ ገብተዋል ተብሏል፡፡

በሁለቱ አገራት መሪዎች ደረጃ በተለያየ ጊዜያት ከኢትዮጵያ ወደ ዑጋንዳ እንዲሁም ከዑጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ጉብኝቶች መካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

የመጀመሪያው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን በዑጋንዳ ካምፓላ፣ ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ አበባ መከናወኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com