በደቡብ አፍሪካ ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ

Views: 110

በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ ታስረው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያላቸው በሙሉ መለቀቃቸውን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት፣ በጆሐንስበርግ ከተማ የሚኖሩ የውጭ አገራት ዜጎች፣ በሕገ-ወጥ መንገድ በተመሳሳይ ምርቶች ንግድ ላይ ተሰማርተዋል በሚል የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ዘመቻ፣ በርካታ ንብረቶች ተወርሰው፤ ሴቶች ተድብድበውና ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች እንደታሰሩ ይታወሳል፡፡

በቀጣይም፣ ኤምባሲው ከመንግሥትና ከዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ጋር በመሆን የዜጎችን ችግሮች በመፍታት፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማሕበር እና የቢዝነስ ማኅበረሰቡ የጀመሩትን የማስተባበር ሥራ የጋራ የምክክር አሰራር እንዲዘረጋ በማድረግ እንደሚደግፍም ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com