ቤተክርስቲያኗ ዘግይታም ቢሆን እየደረሰባት ያለውን ጥቃት ተቃወመች ተባለ

Views: 212

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ እየተከሰተ ባለው  የእርስ በእርስ ግጭት፣ ኹከት እና ብጥብጥ ሳቢያ ለብዙ ዓመት ጥቃት እየደረሰባት ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ዓመትም የሶማሊያው ‹‹ሄጎ›› የተባለው የወጣቶቹ ስብስብ ዒላማውን በጅግጅጋ የምትገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እና ሌሎች ቦታዎችን አድርጎ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም በትንሹ አምስት አብያተክርስትያናት መቃጠላቸው እና በቀሳውስቱ እንዲሁም በዲያቆናት ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሲሆን፣  ከነዚህም ውስጥ አንደኛውን ቄስ በሕይወት እያሉ ማቃጠላቸውም ዘገባው አስታወሷል፡፡

በቅርቡ ደግሞ 11 11 11 በሚል ስያሜ የሲዳማን ክልልነት ያለ ሕገ መንግሥቱ ፈቃድ እና የህዝቡን ይሁንታ ሳያገኝ ‹‹ኤጄቶ›› የተባለው የወጣቶቹ ስብስብ በክልሉ የሚገኙትን አብያተ ቤተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

በዚህም ክስተት አንድ ቄስ መገደላቸው እና ሦስት አብያተክርስትያናት መቃጠላቸው ተሰምቷል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ሲወጡ ስደት ላይ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ በፓትርያርክነት ሲመሩ የቆዩት አቡነ መርቆሬዎስን ጨምሮ የሲኖዶሱ አባል የሆኑ አባቶች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ማረጋቸው የሚታወስ ጉዳይ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com