ዜና

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ

Views: 1075
 • የግንባታው ሥፍራ፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉባ ወረዳ ነው፤
 • የግንባታው የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት እለት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነው፤
 • የዋናው ግድብ ከፍታ – 145 ሜትር
 • የዋናው ግድብ ርዝመት – 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር
 • የዋናው ግድብ ውፍረት – የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን፣ የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር
 • ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን – 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
 • ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት – 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር
 • ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር
 • ግድቡ 16 የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች አሉት፤
 • እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት፤
 • ጠቅላላ ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመነጨው ኃይል መጠን፡- 6 ሽህ 450 ሜጋ ዋት
 • 74 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለው፤
 • ከ 40 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል።
 • ከግድቡ የውሃ ላይ የትራንስፖርት፣ የአሳ ልማት እና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አገልግሎት ይውላል።
 • ታዳሽ ኃይል በመሆን የከባቢ ብክለትን ይከላከላል።
 • አጠቃላይ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ- 66.26 በመቶ ነው ተብሏል፤
 • ግድቡ ሲጠናቀቅም በትልቅነቱ በአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይይዛል።
 • ከታላቁ ህዳሴ ግድብ 16 ኃይል አመንጪ ተርባይኖች መካከል ሁለቱ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ተጠናቀው በድምሩ 750 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫሉ።
 • አሁን ላይ 8ኛ ዓመቱን የያዘውና 98 ቢሊዮን ብር የፈጀው ፕሮጀክቱ፣ ሙሉ ለሙሉ ለመጠናቀቅም ተጨማሪ አራት ዓመታትን ይፈጃል ተብሏል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com