በአዲስ አበባ ልመና እና የወሲብ ንግድ ሊታቀብ ነው

Views: 1811

በአዲስ አበባ ልመና እና የወሲብ ንግድን ለመከላከል ሕግ ሊወጣ ነው፡፡ በቅርቡ የጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ሕግ፣ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ምፅዋት ለሚለምኑ ዜጎች ገንዘብ ወይም ቁሳቁስ የሚሰጡ ሰዎች በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ ነው፡፡

ሕጉ በአዲስ አበባ ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ኗሪዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ሕጉ ከመፅደቁ በፊት በረቂቁ ላይ በየደረጃው ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይትና ምክክር እንደሚደረግበትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታቋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ጎዳና ላይ እየኖሩ መሆኑንን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ናቸው ተብሏል፡፡

በረቂቅ ሕጉ የውይይት መርሃ-ግብር ላይ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመላክተው በጎዳና ከሚኖሩ ዜጎች መካከል 92 ከመቶ ያህሉ ከክልሎች የመጡ ናቸው፡፡

ከእነዚህ መካከልም ከፊሎቹ በልመና የሚተዳደሩ ሲሆን፣ ከፊሎች ደግሞ በወሲብ ንግድ ተግባር መሰማራታቸውን ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com