ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞዛምቢክ መብረር ሊጀምር ነው

Views: 538

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቤይራ- ሞዛምቢክ በሳምንት ሦስት ጊዜ በረራ ሊጀምር መሆኑን አሳወቀ፡፡

አየር መንገዱ፣ መሐል ሞዛምቢክ ወደ ምትገኘው ቤይራ ከተማ በረራውን የሚያደርገው በማላዊ በኩል ሲሆን፣ በመጪው መስከረም 3 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ‹‹በዓለም ላይ ያለንን ተደራሽነት በማስፋት አንደኛ ደረጃ ከተሞችን ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ከተሞችንም መዳረሻችን እያደረግን ነው፡፡

የእርስ በእርስ የትስስር ክፍተቶችን በፍጥነት እየሸፈንን ነው፡፡ በአብዛኛው በረራዎቻችን ቀጥታ ናቸው፤ በመሐል የምናርፍባቸው ቦታዎች ትንሽ ናቸው፡፡ በእነዚህ በትንንሽ ከተሞች ያሉ ደንበኞቻችን 120 በላይ ወደሚሆኑ መዳረሻዎቻችን ሁሉ ሲበሩ ልዩ ጥቅም ይሰጣቸዋል፡፡›› ብለዋል፡፡

ቤይራ፣ አራተኛዋ የሞዛምቢክ ታላቅ ከተማ ስትሆን፣ የንግድ እና የጉብኝት ከተማ በመሆኗ የማዕከላዊ አፍሪካ በር ነች ትባላለች፡፡

ይህ አዲስ በረራ ሲጀመር፣ ወደ ሞዛምቢክ ዋና ከተማ ማፑቶ የሚደረገውን በረራ በማጠናከር ለዓለማቀፍ በረራም እንደሚያግዝ አቶ ተወልደ ገልፀዋል፡፡

በማፑቶ የሚገኘው የኢትዮ-ሞዛምቢክ የጋርዮሽ የአየር መንገድ አገልግሎት ሞዛምቢክ ውስጥ ስምንት መዳረሻዎች አሉት፡፡ ከእነዚህ መካከል ካፑቶ፣ ናምፑላ፣ ቴቴ፣ ፔምባ፣ ቤይራ፣ ናካላ፣ ኩሌማኔ፣ ቪላንኩሎስ እና ቺሞዮ ይጠቀሳሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com