ፖሊስ የራሱን አባላትና የኦሮሚያ ባለሥልጣናትን አሰረ

Views: 100

የፌዴራል ፖሊስ በኦሮሚያ ክልል በተከሰቱ ኹከትና ብጥብጦች ተሳትፈዋል ያላቸውን የፖሊስ አባላት እና የክልሉን የመንግሥት ባለሥልጣናት አሰረ፡፡ ፖሊስ ትናንት ማለዳ ሰባት ተጠርጣሪዎችን ማሰሩን አዲስ ስታንዳርድ የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑትን ጀይላን አብዲን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

እስረኞቹ የተጠረጠሩት ባላፈው ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም በአሮሚያ በተፈፀመው ግድያ ተሳትፈዋል በሚል ነው፡፡ በግድያው የፀጥታ ኃይሎችም ጭምር መሳተፋቸውን አሳሪው ፌዴራል ፖሊስ አብራርቷል፡፡

እስረኞቹ በቅርቡ ወደ አካባቢው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም የገለጹት ኃላፊው፣ ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው ማሕበረሰብ ትብብር መያዛቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ከእስረኞች መካከል ነባር የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የፖሊስ መኮንኖች እንዳሉበት የተጠቀሰ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ቢያንስ አስር ሰዎች በተገደሉበት ግጭት ውስጥ መሳተፋቸውንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ቦርደዴ ወረዳ፣ ጉምቢ ቀበሌ፣ ግምጃ ቤት አካባቢው ባለፈው ነሐሴ ሁለት አንድ ታጣቂ በከፈቱት ተኩስ አንድ ቤተሰብ ውስጥ ብቻ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ቢያንስ አምስት ሰዎች ቆስለዋል፡፡

ክስተቱን ተከትሎ ወደ ቦታው ያመሩት የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ አሁንም በቦታው እየተዘዋወሩ ናቸው፡፡ የአካባቢው ማሕበረሰብም ጥፋተኞችን ለማጋለጥ ከፖሊስ ጋር እየተባበረ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com