ኢትዮጵያ ለውጭ ተቋማት የፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠች

Views: 144

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የውጭ አገራት ባለቤትነት ላላቸው ኩባንያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ባንኩ ፈቃዱን መስጠት የጀመረው ባለፈው ሳምንት ነው፡፡ ይህም በሀገሪቱ ምጣኔ ኃብት ላይ የሚደረገው ለውጥ አካል ነው ተብሏል፡፡

ፈቃዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጭ የሚጠይቁ በመሆናቸው ወደ ሀገር ቤት እንዳይገቡ ተከልክለው የነበሩ ማሽኖች እንዲገቡ ያስችላል ብለዋል የኩባንያ የሥራ ሓላፊዎች፡፡

አፍሪካ አሴት ፋይናንስ ኮምፓኒ የተባለው ታላላቅ ማሽኖችን በማከራየት ሥራ ላይ የተሰማራው የኒው ዮርክ ኩባንያ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ መስጠቱ በኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ምርታማነት እንዲጨምር ያደርጋል ብሏል፡፡

ፍራንስ ቫን ስቻዪክ፣ የአፍሪካ አሴት ፋይናንስ ካምፓኒ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ‹‹በቀላሉ ወደ ገንዘብ ሊቀየር የሚችል የጥሬ ዕቃ እጥረት አለ፡፡ በርካታ ኩባንያዎች የጥሬ ዕቃ እና የማሽኖች ችግሮች አሉባቸው፡፡ ፈቃዱ ይህንን ይቀርፋል፡፡›› ብለዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶክተር) ለሮይተርስ እንደገለፁት፣ ጉዳዩ ከዚህ በፊት ያልተሳኩትን የሕዝብ እና የንግዱ ማሕበረሰብ ፍላጎቶች ለማሳካት ያግዛል፡፡ ይህንን ጉዳይ አጠናክረን እንቀጥላለን፤ በርካታ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል፤ ከፍተኛ የምጣኔ ኃብት ዕድገት እንዲመጣም ያግዛል፡፡ ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com