ሩሲያ በኢትዮጵያ የኃይል ጣቢያ ልትገነባ ነው

Views: 112

ኢትዮጵያና ሩሲያ በኢትዮጵያ የኃይል ጣቢያ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ድርድር ጨርሰው ኮንትራት ሊፈራረሙ እንደሆነ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ እንዳሉት የኃይል ማመንጫ ግንባታውን ለማስጀመር የመጀመሪያ ድርድር ሊጠናቀቅ ሲሆን፣ የግንባታው ቦታ የት እንደሚሆን እስካሁን እንዳልተወሰነም ጠቁመዋል፡፡

በፈረንጆቹ ሰኔ 2017 ዓ.ም የሩሲያው አተም ካምፓኒ እና የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የኑክሌር ኃይልን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀምና በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት እነደተፈራረሙም አስታውሶ የዘገበው ቪ ኦ ፒ ቱደይ ኒውስ ነው፡፡

በሩሲያ መንግሥት በኩል ያለውን የኃይል አቅርቦት ሥምምነት ኹነት ለማካተት፣ የሩሲያ ኤምባሲን ለማነጋገር ብንሞክርም፣ ጉዳዩ ላይ ማብራሪያ መስጠት ሚገባቸው አካላት ሀገር ውስጥ ባለመሆናቸው ለጊዜው ሊሳካ አልቻለም፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com