የኢትዮ-ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ ተጠናቀቀ

Views: 124

ኢትዮጵያ 433 ኪ.ሜ የሚሆነውን የኢትዮ-ኬንያ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ አጠናቀቀች፡፡

ይህ የኤሌክትሪክ መስመር 1955 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን፣ እስከ 2000 ሜጋ ዋት ኃይል መሸከም ይችላል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ መስመር መነሻ ጣቢያው ሥራ 88 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ እስከ ኅዳር 2012 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ቀሪውን 12 በመቶ የሚሆነው ግንባታ እንደተጠናቀቀ ለአምስት ወራት የሙከራ ጊዜ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠናቀቁ፣ ኃይል የማስተላለፍ ሂደቱ ሁለቱ አገራት ባደረጉት የውል ስምምነት መሠረት እንደሚደረግም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ለኤሌክትሪክ ማሰራጫው መስመርና ለኤሌክትሪክ መስመር መነሻ ጣቢያ ግንባታ 333 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዳወጣ ተነግሯል፡፡

ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት የምስራቅ አፍሪካ አገራት በኤሌክትሪክ መስመር እንዲገናኙ የማድረግ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል፡፡

ወደ ፊት በኢትዮጵያ የተጀመሩ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ሲጠናቀቁ ለታንዛንያ፤ ኡጋንዳ እና ለሌሎች አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል የመስጠት ዕድል እዳለም ታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com