“ቺኩንጉንያ” በትንኝ የሚተላለፍ በሽታ በድሬዳዋ ተከሰተ

Views: 393

በድሬደዋ አስተዳደር የ“ቺኩንጉንያ” ወረርሽን ምልክቶች በ3 ሺህ 756 ሰዎች ላይ መታየቱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

“ቺኩንጉንያ” ቫይረስ በትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ድንገት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህመምን ያስከትላል ተብሏል፡፡

እስካሁን በአስር ናሙናዎች ላይ በተደረገ ምርመራ አራቱ በ“ቺኩንጉንያ” መያዛቸው ስለተረጋገጠ ወረርሽኝ ሁኖ ተከስቷል ያሉት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፉአድ ከድር ናቸው፡፡

በተጨማሪም፣ ቺኩንጉንያ በሽታ ከወባ እና ደንጌ ከሚባል በሽታ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው ሁሉም ታማሚዎች በ“ቺኩንጉን” ስለመያዛቸው ሙሉ በሙሉ እንዳልተረጋገጠ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ከበሽታው ጋር በተያያዘ እስካሁን የተመዘገበ ሞት እንደሌለ ዶ/ር ፉአድ ጠቁመው ቢሮውም የተከሰተውን ወረርሽን ለመከላለከል እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ወረርሽኙ በየት አካባቢ በብዛት እንደተዛመተ የድሬደዋ ከተማ መስተዳደር የህዝብ ግንኙነት የሥራ ሂደት አባል ወ/ሪት ቤዛዊት ተሾመን ዘጋቢያችን በስልክ ያነጋገረች ሲሆን ‹‹የጤና ቢሮ ባለሟል አነጋግሬ ዝርዝሩን አሳውቃችኋለሁ›› ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com