የአዲሰ አበባ ሆቴሎች ዋጋ ውድ መሆን እያነጋገረ ነው

Views: 210

በአፍሪቃ ከሚገኙ ሆቴሎች ውስጥ በዋጋ ውድ ናቸው ከተባሉት አገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ጥናቶች አመላከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ሆቴሎች ዋጋ ሀገር ጎብኚ (ቱሪስት) የሚያስቆይ አይደለም ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ለመሠረተ-ልማት በሰጠችው አትኩሮት፣ በማደግ ላይ ካሉ የአፍሪቃ አገራት አንዷ ናት ሲል የገለጸው ዓለማቀፍ ጥናት፣ ከአፍሪካ አገራት ‹‹አዲሷ ቻይና›› እየተባለች መሆኗን ጠቁሟል፡፡

ለአንድ ዓመት ያህል በተደረገው ተከታታይ ጥናት፣ በአዲስ አበባ በቀን 163 ነጥብ 79 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ 4,740 ብር በላይ የሚያስወጣ ሲሆን፣ በየዓቱም የ1 ነጥብ 1 በመቶ ዋጋ እንደሚጨምር የSTR ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡

የከተማይቱ ሆቴሎች ዋጋ ውድ መሆኑን በምክንያትነት የተጠቀሱት በከተማዋ ብዙ ፍላጎቶች ያሉባት መሆን፤ በተለይ የኢኮኖሚ ዕድገቱ የራሱ ሚና እንዳለው የተጠቀሰ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጤታማ መሆን ደግሞ ትልቁ ዋቢ ነው ሲል ጥናቱ በውጤት ግኝቱ ላይ አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪም አዲስ አበባ በአፍሪካ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ኹነቶች በብዛት የሚከወንባት ከተማ መሆኗም ሌላው ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

የጋናዋ ከተማ አክራ እና የናይጄሪያ ሌጎስ ከአዲሰ አበባ በመቀጠል በሆቴሎች ውድነት ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ነው ሲል ይኸው ጥናት አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በፍጥነት ኢኮኖሚያቸው እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙት አገራት መካከል መግባቷ ተገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪው ዘርፍ፣ የመሠረተ-ልማት ግንባታ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ብዙ በመሰራቱ  ለኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ አደርጓል ሲል የጥናቱ ሃቲት ይገልፃል፡፡

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በፊት በዓለም ላይ ደሀ ከሚባሉት አገራት መካከል በሦስተኛ ደረጃ መቀመጧን እና ከ50 በመቶ በላይ የሆኑ ዜጎቿ ደግሞ ከድህነት ወለል በታች ይኖሩ ነበር፡፡

አሁን ግን ሀገሪቱ ከአፍሪካ አገራት  የፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗን  እና በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ሁለተኛ መሆኗም ኢንቨስትመንትን ወደ ሀገሯ እየሳበ ነው ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com