የኢትዮጵያ ማኅበራዊ የሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር እንቀስቃሴ ቅኝት ተደረገ

Views: 118

ኢትዮጵያ በቅርቡ የዓለም ማህበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር ፎረም በአዲሰ አበባ ታዘጋጃለች፡፡ እስካሁን 55 ሺህ የሚጠጉ የማህበራዊ የሥራ ፈጠራ ተቋማት እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ማህበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር፣ አዎንታዊ የሆነ ማሕበራዊ ለውጦችን እንዲኖር ያርደጋል ነው የተባለው፡፡

ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው ፎረም ላይ ልምድ ለመለዋወጥ እና የቴክኖሎጂ ልምድ እንዲደብር የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል፡፡

አንዱ ሀገር ከሌላው ጋር ያለውን ግንኙነት ከማጠናር በተጨማሪ፣ ከአንድ ሺህ 200 በላይ ልዑካኖች እንደሚገኙም ይጠበቃል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የፎረሙ ቅድመ ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል፤ ለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ማህበራዊ የሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር ተናበው ሥራቸውን እያከናወኑ ይገኛል ተብሏል፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል እንዳስታወቀው፣ ማሕበሩ በወጣቶች እና በወጣት ሴቶች የሚመራ ነው፡፡

75 በመቶ የሚሆኑት የማሕበራዊ ስራ ፈጣሪዎች ኢንተርፕራይዞች የተመሰረቱት በ2010 ዓ.ም ሲሆን፣ መስራቾቹ ደግሞ 35 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያው ከ35 ዓመት በታች ነው ሲል አስታውቋል፡፡ ማህበራቱ 28 በመቶ የሚመሩት ደግሞ በሴቶች መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሰዎች አዳዲስ ሥራን እንዴት መፍጠር እንደሚችሉ በቀላሉ መንገድ ለማሳየት እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡

ቀደም ሲል ይህ ፎረም በስኮትላንድ ኤደንብራ ከተማ በፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም ተካሂዶ እንደ ነበር ተገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com