ብራና ግጥም በጃዝ ወርኃዊ የግጥም ምሽት ዛሬ ይካሄዳል

Views: 234

“የት ነው የደረስነው?” በሚል ርዕስ ወርኃዊው ብራና ግጥም በጃዝ የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 6 ቀን ከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡

በምሽቱ የጥበብ መርሃ-ግብር፣ አንጋፋ የጥበብ ባለሟሎች ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ከጥበብ ዘርፍ ውጪ ያሉ ባለሟሎችም በመድረኩ ላይ ሃሳባቸውን የሚያካፍሉበት መርሃ-ግብር ተይዟል ነው የተባለው፡፡

ከታሪክ ባለሟል አንጋፋው ደራሲ፣ የሥነጽሑፍ መምህር እና የታሪክ ፀሐፊው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶላሳ፣ ከስፖርት ባለሟሎች ደግሞ ዓለማቀፍ የእግር ኳስ ዳኞች ኢንስትራክተር ባምላክ ተሰማ እና ኢንስትራክተር ሊዲያ ታፈሰ በመድረኩ ላይ ይሳተፋሉ፡፡

በእለቱ የግጥም ሥራዎቻቸውን ከሚያቀርቡት የጥበብ ባለሟሎች መካከል ደግሞ ነብይ መኮንን፣ ዮሐንስ ገ/መድህን እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com