ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች ገቢዋ እየቀነሰ መጥቷል ተባለ

Views: 121

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶቿ የምታገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በአንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ዶላር እንደወረደ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ሀገሪቷ የውጭ ንግድ አፈፃፀሟ ከ2012 እ.ኤ.አ ጀምሮ እየቀነሰ መምጣቱም ተጠቁሟል፡፡

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሀገሪቷ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶቿ በአጠቃላይ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢን ያገኘች ሲሆን፣ ወደ ውጭ ከተላኩት ምርቶች ውስጥ ደግሞ 74 በመቶ የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከግብርና ምርቶች ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ምርቶቿን ከምትልክባቸው 146 አገራት ውስጥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አሜሪካ ከሁለት መቶ ሰማንያ ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለውን ምርት ከኢትዮጵያ በማስገባት ከፍተኛውን ድርሻ እንደያዘች ተነግሯል፡፡

ከአሜሪካ በመቀጠል ጎረቤት አገር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ምርቶችን በማስገባት ሁለተኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን፣ ኔዘርላድ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ ጀርመን፣ ጃፓን እና እስራኤል በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸው ዋነኛ ምርቶችዋ ቡና፣ ጫት፣ አበባ፣ ሚኒራሎች፤ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬና እህል፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ሻይ ቅጠል፣ ማር፣ ወተትና የወተት ተዋፅዎች፣ አሳ፣ ስጋ፣ የቁም ከብቶች እንዲሁም የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆች፣ መድኃኒቶች፣ የቆዳ ውጤቶች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ ኬሚካሎች እና የግንባታ ግብዓቶች ናቸው ሲል የዘገበው ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com