የእግርኳስ ተጫዋቾች ወርሃዊ የደሞዝ ጣሪያ 50 ሺህ ብር እንዲሆን ተወሰነ

Views: 106

የኢፌድሪ ስፓርት ኮሚሽን ከኢትዮጽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተጫዋቾች ወርሃዊ የደሞዝ ጣሪያ ላይ ያተኮረ ውይይት በቢሾፍቱ ከተማ አካሄደ።

በዉይይቱ አቶ ተድላ ዳኛቸዉ የሀገራችንንና የሌሎች ሀገራትን የተጨዋቾች የደሞዝ አከፋፈልን በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል ።

ጥናታዊ ፅሁፉን መነሻ በማድረግ የተጫዋቾችን የደሞዝ ጣሪያ ማስቀመጥ ከሀገር ፣ ከተጫዋቾች እና ከክለብ አንፃር ያለው ጠቀሜታ፣ ተግዳሮትና አማራጮች ላይ ዉይይት ተደርጓል።

የተጫዋቾች የደሞዝ ጣሪያ መቀመጡ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማፍራት፣ የገንዘብ ብክነትን ለመቀነስ፣ ተመጣጣኝ የሆኑ ክለቦች እንዲኖሩ ለማድረግ፣ ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲሰፍን ለማድረግ፣ ሌሎች ስፓርቶችን ለመደገፍ ስለሚያግዝና ብቁና ተፎካካሪ ተጫዋቾችን ለማፍራት ስለሚጠቅም ጣሪያዉ መቀመጡ ወሳኝ ነው ተብሏል ።

ዉሳኔዉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ወር ጀምሮ በመመሪያ በማስደገፍ እንዲያስፈፅም አቅጣጫ እንደተቀመጠ የወጣቶችና ስፓርት ሚኒስትር አስታውቋል።

አሁን አሁን በፋይናንስ ችግር ሊፈርሱ የቻሉ ክለቦች ሁሉ ከፍተኛ ደሞዝ ከፋይ እንደነበሩ የሚታወቅ ነዉ።

ለአብነትም ደደቢት እግርኳስ ክለብ ለአጥቂው ጌታነህ ከበደ በወር ከአንድ መቶ ሺህ ብር በላይ ይከፍል እንደነበር የሚታወስ ነው ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com